Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ ከ68 ሚሊየን ብር በላይ ከምዝበራ ማዳን መቻሉ ተገለጸ

 

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በተከናወነ ሙስናን የመከላከል ጥረት ከ68 ሚሊየን ብር በላይ የመንግሥትና የህዝብ ሃብት ከምዝበራ ማዳን መቻሉ ተገልጿል፡፡

የክልሉ ሥነ-ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽ ኮሚሽነር ሙሉሰው ዘውዴ÷ የመንግሥት ተቋማትና ህዝባዊ የልማት ድርጅቶች ከሙስናና ብልሹ አሰራር በፀዳ መልኩ ሥራቸውን እንዲያከናወኑ ክትትል ሲያደርግ መቆየቱን ገልጸዋል።

ኮሚሽኑ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ባደረገው ጥረት በአስቸኳይ ሙስና መከላከል ስራ ከ17 ሚሊየን ብር በላይ ማዳን መቻሉን ነው የተናገሩት፡፡

እንዲሁም በአሰራር ጥሰት ሊባክን የነበረና በኦዲት ግኝት የተረጋገጠ ከ51 ሚሊየን ብር በላይ ማስመለስ መቻሉን አንስተዋል።

ያለ አግባብ የተያዘ ከ2 ሺህ 213 ሄክታር በላይ የገጠርና ከ29 ሺህ 766 ካሬ መሬት በላይ የከተማ መሬት ማስመለስ መቻሉን መናገራቸውንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ኮሚሽኑ የተለያዩ የጥቆማ መቀበያ ዘዴዎችን በመዘርጋት 519 ጥቆማዎችን መቀበሉን ገልጸው÷ ከዚህ ውስጥ 342 ያህሉ አስተዳደራዊ ውሳኔ ማግኘቱን ጠቁመዋል።

134 ጥቆማዎችን በማስረጃ በማረጋገጥ እና በመተንተን ለፍትሕ አካላት ማስተላለፍ መቻሉንና የተቀሩት ጥቆማዎች ደግሞ በሒደት ላይ መሆናቸውን ኮሚሽነሩ ገልጸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.