የግብርና ግብዓቶችን በተገቢው ጊዜ ለማሰራጭት እየተሰራ ነው – አቶ አወል አርባ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል የግብርና ግብዓቶችን በተገቢው ጊዜ ለማሰራጭት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገለጹ፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ የግብርና ግብዓቶችን ከውጭ ለማስገባት የተመቻቸውን እድል በመጠቀም በማህበር ተደራጅተው የሚሰሩ ዩኒየኖችን ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝታቸውም ጋሊኮማ የተሰኘውን የግብርና ግብዓት አቅራቢ ማህበር የሥራ እንቅስቃሴን ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡
በዚህ ወቅትም በአፋር ክልል የግብርና ግብዓቶችን ለአርሶ አደሩ በተገቢው ጊዜ ለማሰራጨት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በክልሉ የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን ከግብ ለማድረስ ተግዳሮት የነበረው የግብርና ግብዓት አቅርቦት ችግር ምላሽ እያገኘ መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡
ይህም የክልሉን የልማት ሥራዎች ለማበረታታት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ነው አቶ አወል አጽንኦት የሰጡት፡፡