Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ወጣቶችን በማብቃት 2 ሚሊየን አዳዲስ ሥራዎችን ለመፍጠር አቅዳለች- ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ትምህርትን ተደራሽ በማድረግ ብሎም ወጣቶችን በማብቃት ኢትዮጵያ 2 ሚሊየን አዳዲስ ሥራዎችን ለመፍጠር አልማለች ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመራ ልዑክ በዓለም አቀፉ የልማት ማኅበር (አይ ዲ ኤ) 21ኛ የማሟያ ጉባዔ ላይ እየተሳተፈ ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው÷የኢትዮጵያ በፈተናዎች ሁሉ የተሻገረ ያለመበገር ፅናት የምጣኔ ሃብት መረጋጋትን እና ምርታማነትን ባስቀደሙት በመዋቅራዊ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሥራዎቿ ማሳያነት ይገለጣል ብለዋል።

በብሔራዊ የምክክር ኮሚሽን በሚመራው ሥራ ምክክር እና እርቅ የሰላም ፍላጎታችን እና ተምኔታችን ማጠንጠኛ ናቸው ሲሉም ገልጸዋል፡፡

ትምህርትን ተደራሽ በማድረግ ብሎም ወጣቶችን በማብቃት ኢትዮጵያ 2 ሚሊየን አዳዲስ ሥራዎችን ለመፍጠር ማለሟንም ጠቅሰዋል፡፡

ኢትዮጵያ አረንጓዴ አሻራን በመሰሉ ንቅናቄዎች ሃይልን ለሁሉም ማዳረስ፣ የዲጂታል ሽግግር እና የተፈጥሮ ከባቢን የመንከባከብ ተግባራትን ለመከወን ትኩረት ትሰጣለች ነው ያሉት።

የዓለም አቀፍ የልማት ማኅበር ለአሕጉሩ ድጋፉን እንዲያጠናክር ኢትዮጵያ ጥሪ ታቀርባለችም ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.