Fana: At a Speed of Life!

ትንሳኤን ስናከብር ለተቸገሩ ያለንን በማካፈል ይሁን- አቶ ጌታቸው ረዳ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የትንሳኤን በዓል ስናከብር በተፈጥሮና ሰው ሠራሽ አደጋዎች ለችግር ለተጋለጡ ወገኖች ያለንን በማካፈል ሊሆን ይገባል ሲሉ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አሥተዳደር ርዕሰ መሥተዳደር ጌታቸው ረዳ ገለጹ፡፡

አቶ ጌታቸው በዓሉን ምክንያት በማድረግ ለክርስትና ሐይማኖት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈው፡፡

በመልዕክታቸውም÷ የትንሳኤን በዓል ከሕዝባችን ጋር ተካፍለንና ተባብረን ልናሳልፈው ይገባል ሲሉ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

በዓሉን ስናከብርም በተፈጥሮና ሰው ሠራሽ አደጋዎች ለችግር የተጋለጡ ወገኖችን በመርዳትና ያለንን በማካፈል ሊሆን ይገባል ነው ያሉት፡፡

በዓሉን በሰላምና በፍቅር ማሳለፍ እንደሚገባም አመላክተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.