Fana: At a Speed of Life!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሌማት ትሩፋት ተሞክሮዎችን የማስፋት ሥራ መጀመሩ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሌማት ትሩፋት ተሞክሮዎችን በሁሉም ወረዳዎች የማስፋት ሥራ መጀመሩን ርዕሰ መሥተዳድር አሻድሊ ሃሰን ገለጹ።

የእንስሳት እና የተፈጥሮ ሀብትን በተገቢው መንገድ ለመጠቀም የሌማት ትሩፋት መልካም አጋጣሚ መፍጠሩንም የገለጹት አቶ አሻድሊ÷ በ50 ሚሊየን ብር በኡራ ወረዳ የተገነባው ኸሉዋ የተቀናጀ የእስሳት እርባታ ማዕከል አንዱ ማሳያ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

በማዕከሉም ዶሮ፣ የወተት ላሞች፣ ዓሣ፣ ንብ ዕርባታን ጨምሮ የእስሳት መኖ ማቀነባበሪያ መኖሩን ገልጸው÷ ይህም ለኅብረተሰቡ እንስሳትና የእንስሳት ተዋጽኦዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ ማስቻሉን ጠቅሰዋል፡፡

በመንግስት ከተከናወኑ የሌማት ትሩፋት ተግባራት በተጨማሪ ኅብረተሰቡ በስፋት በመርሐ-ግብሩ በፈቃደኝት በመሳተፍ ኑሮውን እየቀየረ መሆኑንም ነው ለኢዜአ የተናገሩት፡፡

እንደ ሞዴል በክልሉ የተሠራው የሌማት ትሩፋት ማዕከል ተሞክሮ ወደ ሁሉም የክልሉ ወረዳዎች በማውረድ የክልሉን የእንስሳት እና ተፈጥሮ ሀብት በሚገባ ለማልማት መታቀዱንም አመላክተዋል፡፡

በሌማት ትሩፋት መርሐ-ግብሩ የሚገነቡት አዳዲስ ኢንዱስትሪዎች የኅብረተሰቡን የእንስሳት ተዋጽኦ ፍላጎት ከማሟላት ባሻገር ምርትን ወደ ውጪ የመላክ ዕቅድ እንዳላቸውም ነው ያስታወቁት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.