Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያና እና ኮንጎ ኪንሻሳ መካከል የአየር ትራንስፖርቱን ለማሳለጥ ያለመ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኮንጎ ኪንሻሳ የትራንስፖርትና ኮሙኒኬሽን ሚኒስትር አማካሪ ሙሴንጌዚ ኪታሳ የተመራ የአቪዬሽን ልዑክ ከኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን አመራሮች ጋር የአየር ትራንስፖርቱን ለማሳለጥ ያለመ ምክክር አካሂዷል፡፡

በምክክራቸውም ለሁለቱ ሀገራት በተዘጋጀው የአየር ትራንስፖርት የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት ላይ መወያየታቸው ተገልጿል፡፡

በውይይቱ የተደረሰውን ስምምነት ተከትሎ የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የአየር ትራንስፖርቱን ለማሳለጥና የበረራ መዳረሻዎችን ለማሳደግ የሚያስችለውን የአየር ትራንስፖርት ስምምነት ከኮንጎ ኪንሻሳ ጋር ነገ እንደሚፈራረሙ ተጠቁሟል፡፡

የፊርማ ሥነ-ሥርዓቱም የውጭ ጉዳይና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት እንደሚከናወን መገለጹን የባለስጣኑ መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.