Fana: At a Speed of Life!

ከጣና ሐይቅ እምቦጭ አረምን ለማስወገድ ያለመ ንቅናቄ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጣና ሐይቅ ላይ ያለውን የእምቦጭ አረም ለማስወገድ ያለመ ንቅናቄ መጀመሩን የጣናና ሌሎች የውሃ አካላት ልማትና ጥበቃ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች፣ የጣና እና ሌሎች የውሃ አካላት ልማትና ጥበቃ ኤጀንሲ እንዲሁም የባህርዳር ከተማ አስተዳደር አመራሮች በጉዳዩ ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱም በክልሉ ካለፈው ሐምሌ ወር 2015 ዓ.ም ጀምሮ በነበረው የሠላም እጦት ምክንያት የእምቦጭ አረም በጣና ሐይቅ ላይ መስፋፋቱ ተመላክቷል፡፡

በሐይቁ ዙሪያ ያለውን አረም ለማስወገድም በቀጣይ ወራትቶች የሚተገበር መርሐ ግብር መዘጋጀቱ ነው የተገለጸው፡፡

በዚህ መሰረትም በሐይቁ ዙሪያ ያለውን ማህበረሰብ በማሰማራት አረሙን ለማስወገድ የሚያስችል ንቅናቄ በዛሬው ዕለት መጀመሩ ተጠቁሟል፡፡

ለዚህ ተግባር ስኬትም የሚመለከታቸው አካላት እና የአካባቢው ማህበረሰብ በንቃት እንዲሳተፍ ኤጄንሲው ጥሪ አቅርቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.