Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ ከአፍሪካ ቀንድ ሀገራት መሪዎች ጋር በመሆን በጅቡቱ ችግኝ ተከሉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከአፍሪካ ቀንድ ሀገራት መሪዎች ጋር በመሆን በጅቡቱ ችግኝ ተከሉ።

በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ላይም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የጂቡቱ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ፣ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ፋርማጆ እና የሶማሊ ላንድ ፕሬዚዳንት ሙሳ ቢሂ አብዲ ተሳትፈዋል።

ችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩን አስመልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በፌስቡክ ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት፥ “የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት መሪዎች ከሆኑ ወንድሞቼ ጋር ችግኞችን ተክለናል” ብለዋል።

“ፕሬዚደንት ኢስማኤል ኦመር ጊሌ አረንጓዴ ዐሻራ በጅቡቲ እንዲከናወን በማድረጋቸው አመሰግናቸዋለሁ” ሲሉም ገልፀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ እና የልዑካን ቡድናቸው በሶማሊያ እና በሶማሌላንድ ግንኙነት ዙሪያ በሚደረገው የምክክር መድረክ ላይ ለመሳተፍ ዛሬ ጅቡቲ መግባታቸው ይታወቃል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.