Fana: At a Speed of Life!

የዳያስፖራው ማኅበረሰብ ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አንድ አቋም ሊኖረው ይገባል-የኢትዮጵያ ዳያስፖራዎች ማኅበር

አዲስ አበባ፣ ሀምሌ 12፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዳሴውን ግድብ አስመልክቶ የዳያስፖራው ማኅበረሰብ አንድ አቋም ሊኖረው እንደሚገባ የኢትዮጵያ ዳያስፖራዎች ማኅበር ገለጸ።

ማኅበሩ የአሜሪካ መንግሥት በግድቡ ላይ ገለልተኛ አቋም እንዲኖረው ሲሰራ መቆየቱም አስታውቋል።

ኢትዮጵያዊያን በራሳቸው አቅም የሚገነቡት ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ወደ መጨረሻው ምዕራፍ  ላይ ከመድረሱም ባለፈ ÷ የዳያስፖራ ማኅበር አባላቱ ግድቡ በውጭው ማኅበረሰብ ዘንድም እንደ ዓይን ብሌን የሚታይ  በመሆኑ ወቅቱ ያለ ልዩነት ድጋፍ የምናደርገበት ነው ሲሉ ተደምጠዋል።

የማኅበሩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አብርሃም ስዩም÷ኢትዮጵያዊያን ከጫፍ እስከ ጫፍ የተንቀሳቀሱበት ጉዳይ ቢኖር የሕዳሴው ግድብ ነው ብለዋል ።

ግድቡ የሕይወትና የሉዓላዊነት ጉዳይ በመሆኑ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በዚህ ሊደራደር እንደማይገባም አመልክተዋል።

አቶ አብረሃም አያይዘውም “ፖለቲካና ልማትን መለየት ያስፈልጋል” ልዩነት ያለና የሚጠበቅ ቢሆንም ዓባይ ላይ ሁላችንም አንድ አቋም ሊኖረን ያሻል ነው ያሉት ።

እንደ አቶ አብርሃም ገለጻ ግድቡ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ስለደረሰ የውጭው ማኅበረሰብ ከጫፍ ጫፍ ሊንቀሳቀስ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

 

ከዚያም ባለፈ በአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እየተደረገ ስላለው ንቅናቄም አብራርተዋል።

የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ “ዳግማዊ አድዋ ነው” ያሉት ደግሞ የማኅበሩ የቦርድ አባል አቶ እድሪስ መሀመድ ናቸው።

ሌላው የማኅበሩ የቦርድ አባል ሻምበል ብርሃኑ ተስፋዬም በውጭ ያለው ማኀብረሰብ ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርግ በቅርበት መስራት ያስፈልጋል የሚል ሀሳብ አንስተዋል።

“በውጭ ላለው ማኅበረሰብ ስለ ግድቡ ተገቢውን ቅስቀሳ በማድረግ ማሳተፍ ይገባል” ያሉት ሻምበል ተስፋዬ ዳያስፖራው እንደ ሌላ አካል መታየት የለበትም ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.