Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ የአጭር፣ መካከለኛ፣ የእርምጃና የሜዳ ተግባራት አትሌቲክስ ውድድር መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ የአጭር፣ መካከለኛ፣ የ3000 ሜትር መሰናክል፣ የእርምጃ እና የሜዳ ተግባራት አትሌቲክስ ውድድር እየተካሄደ ነው።

አትሌቲክስ ውድድሩ በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ስታዲየም መካሄድ መጀመሩን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ባወጣው መረጃ አስታውቋል።

በዛሬው እለትም የአሎሎ ውርወራ ማጣሪያና ፍፃሜ፣ የስሉስ ዝላይ ማጣሪያና ፍፃሜ ውድድሮች እንደሚካሄዱ የወጣው መርሃ ግብር ያመለክታል።

እንዲሁም ከ100 ሜትር እስከ 800 ሜትር የማጣሪያ ውድድሮች እንደሚካሄዱ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.