Fana: At a Speed of Life!

ጨፌ ኦሮሚያ 12ኛ መደበኛ ጉባዔውን ነገ እና ከነገ በስቲያ ያካሂዳል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ ) ጨፌ ኦሮሚያ 12ኛ መደበኛ፣ 5ኛ ዓመት 5ኛ የሥራ ዘመን ጉባዔውን ነገ እና ከነገ በስቲያ ያካሂዳል፡፡

የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባዔ ወይዘሮ ሎሚ በዶ ጨፌው በሁለት ቀን ውሎው የ2012 ዓ.ም የሥራ አፈፃፀም እንደሚገመግም ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም የ2013ን በጀት ተወያይቶ እንደሚያፀድቅም ጠቁመዋል።

እንዲሁም የጨፌ ኦሮሚያ 11ኛ ቃለ ጉባኤ ያፀድቃል ተብሎም ነው የሚጠበቀው፡፡

የክልሉን የውሃና ፍሳሽ አዲስ ረቂቅ አዋጅ ማጽደቅም የጉባኤው አጀንዳ ነው ተብሏል፡፡

በተጨማሪም የሕግ ማርቀቅ እና በተጓደሉ አመራሮች ቦታ ሹመት እንደሚያጸድቅ ከጨፌ ኦሮሚያ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.