Fana: At a Speed of Life!

ኢ/ር ታከለ ኡማ ከውሀ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ኢንጅነር ስለሺ በቀለ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 9፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ከውሀ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ ጋር ተወያይተዋል።

በዚህ ወቅትም የከተማ አስተዳደሩ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር በጋራ መስራት በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

በከተማዋ የንፁህ መጠጥ ውሀ አቅርቦት ላይ በጋራ መስራት በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ እና በከተማ አስተዳደሩ ለመስራት የታሰቡና እየተከናወኑ ያሉ የውሀ ፕሮጀክቶችን ለመደገፍ በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።

ድጋፎቹ አዳዲስ ፕሮጀክቶችን ለማስጀመር የፋይናንስ ምንጭን ማፈላለግና የቴክኒክ ድጋፍ ማድረግን ያካትታሉ።

በተጨማሪም በከተማዋ ያለውን የኤሌክትሪክ ሽፋን ማሳደግ በሚቻልባቸው መንገዶች በጋራ ለመስራትም ተስማምተዋል።

የከተማ አስተዳደሩ በትኩረት እያከናወነ የሚገኘው የከተማ ግብርና በመስኖና በተለያዩ የውሀ አማራጮች በማመቻቸትና ቴክኒካዊ ድጋፎች ላይ ለመስራት መስማማታቸውንም ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በተጨማሪም የፍሳሽ አወጋገድ ላይ የከተማ አስተዳደሩ እያከናወናቸው ያሉ ተግባራትን መደገፍ በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያና በተለያዩ የጋራ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.