Fana: At a Speed of Life!

ሀገር አቀፍ የወጣቶች ጤና ፎረም ሊካሄድ ነው

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 13 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ሀገር አቀፍ የወጣቶች ጤና ፎረም ሊካሄድ መሆኑን አስታወቁ፡፡

መድረኩ ወጣቶች በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚዘጋጁ የጤና ፖሊሲዎች እና ፕሮግራሞች ላይ የሚወያዩበት እንዲሁም ያሏቸውን አመለካከቶችና የመፍትሄ ሃሳቦች የሚያቀርቡበት መድረክ መሆኑንም በፌስ ቡክ ገጻቸው አስታውቀዋል፡፡

ጤና የሁሉም ነገር መሠረት መሆኑን ያነሱት ሚኒስትሯ ስለ ጤናችን እናውራ፣ እንነጋገር እንዲሁም ዘላቂ የሆነ መፍትሔ እንፈልግለት ብለዋል፡፡

ሚኒስትሯ ለወደፊት ጤናችን ዕናቅድ፣ እንወያይ፣ እንተግብርና ለውጥ እናምጣ ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የመጀመሪያው የሀገር አቀፍ የወጣቶች ጤና ፎረም ነገ የሚካሄድ ይሆናል፡፡

መሳተፍ የሚፈልጉ ወጣቶችም ከታች በተጠቀሱት አድራሻዎች በመግባት መመዝገብ ይችላሉ፡፡

https://eyhf.eventbrite.com/ ወይም
http://ethioyouth.org/

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.