Fana: At a Speed of Life!

ካርሎ አንቸሎቲ የኤቨርተን አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 11፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የእንግሊዙ እግር ኳስ ክለብ ኤቨርተን አሰልጣኝ ካርሎ አንቸሎቲን የክለቡ ዋና አሰልጣኝ አድርጎ መሾሙን አስታወቀ።

ኤቨርተን ጣሊያናዊውን አሰልጣኝ ካርሎ አንቼሎቲን በ4 ዓመት ከግማሽ ኮንትራት ነው የክለቡ አሰልጣኝ በማድረግ የቀጠረው።

በያዝነው የፈረንጆቹ ወር የመጀመሪያ ላይ ከናፖሊ የተሰናበቱት አሰልጣኝ ካርሎ አንቸሎቲ ከሁለት ሳምንት በፊት ከጉዲሰን ፓርክ የተሰናበቱትን አሰልጣኝ ማርኮ ሲልቫን ተክተው ነው ክለቡን የሚረከቡት።

ሶስት ጊዜ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ያነሱት አሰልጣኝ ካርሎ አንቸሎቲ ቸልሲ ካሰናበታቸው ከ8 ዓመት ተኩል በኋላ ነው ወደ እንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የተመለሱት።
ኤቨርተንን በመቀላቀላቸው መደሰታቸውን የገለጹት አሰልጣኝ ካርሎ አንቸሎቲ፥ ክለቡ ውጤት በመፈለጉ ወደዚህ እንዳመጣቸውም ገልፀዋል።

ኤቨርተን በዛሬው እለት ማይክ አርቴታን አዲሱ አሰልጣኝ አድርጎ ከሾመው ከአርሰናል ጋር ከሚኖረው የፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ቀደም ብሎ ነው ካርሎ አንቸሎቲን አሰልጣኝ አድርጎ መሹሙን ያስታወቀው።

አሰልጣኝ ካርሎ አንቸሎቲ በዛሬው እለትም በጉዲሰን ፓርክ ተገኝተው ኤቨርተን ከአርሰናል የሚያደርገውን ጨዋታ የሚመለከቱ ሲሆን፥ በነገው እለትም ክለቡን በይፋ እንደሚረከቡን ተገልጿል።

የ60 ዓመቱ ጣሊያናዊው አሰልጣኝ የመጀመሪያ ጨዋታቸውንም በቀጣይ ሳምንት ኤቨርተን ከበርንለይ በሚያደርገው ጨዋታ ስራቸውን ይጀምራሉም ተብሏል።

ምንጭ፦ www.bbc.com/sport

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.