189 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ተመለሱ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)189 ኢትዮጵያውያን ዛሬ ከቤሩት ወደ አገራቸው ተመለሱ፡፡
ዛሬ ከቤሩት ወደ ሃገራቸው የተመለሱት 189 ኢትዮጵያውያን ሰነድ አላባ መሆናቸው ታውቋል፡፡
ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ ሰነድ አልባ ዜጎችን ወደ አገራቸው የመመለሱ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ከቤሩት የኢትየጵያ ቆንስላ ጄኔራል ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ፡፡