ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በንፁሃን ላይ የተፈፀመውን ጥቃት አወገዙ
አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የተፈፀመውን ጥቃት አውግዘዋል።
ዘርና ሀይማኖት ለፖለቲካ ጥቅም እንዲውሉ ሲደረግ፤ ንጹሀን ዜጎች በአሰቃቂ ሁኔታ ሲገደሉ፣ ሲፈናቀሉና ሲንከራተቱ ማየት ስሜትን ለመግለጽ ቃላት ያጥራል፤ ለቅሶ፣ድንጋጤና ሥጋት የብዙዎችን በር አንኳኩቷል ሃዘናቸው ሃዘኔ ነው ብለዋል:
ሀገሪቱን ካንዣበበባት ክፉ አደጋ ለማዳን ሁሉም ሚናውን ሊወጣ ይገባልም ነው ያሉት ።