Fana: At a Speed of Life!

ፍርድ ቤቱ አቶ ልደቱ አያሌው መከላከያ ማስረጃ እንዲያቀርቡ ብይን ሰጠ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አቶ ልደቱ አያሌው በተከሰሱበት ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት ወንጀል መከላከያ ማስረጃ እንዲያቀርቡ ፍርድ ቤቱ ብይን ሰጠ።
 
የኦሮሚያ ከልል የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባለፈው ቀጠሮ የተሰማውን የዐቃቤ ህግ ምስክር ማስረጃን መርምሮ ብይን ለመስጠት ለዛሬ በያዘው ተለዋጭ ቀጠሮ መሰረት ተሰይሟል፡፡
 
በዚህ መሰረት ፍርድ ቤቱ አቶ ልደቱ በተከሰሱበት ወንጀል ዐቃቤ ህግ ያሰማቸውን ምስክሮች መከላከል የሚያስችል የመከላከያ ማስረጃ ካላቸው እንዲያቀርቡ ለህዳር 16 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
 
ፍርድ ቤቱ ለአቶ ልደቱ በዚህ ክስ የ100 ሺህ ብር ዋስትና መፍቀዱ የሚታወስ ነው።
 
ህገ መንግስቱን በኃይል ለማፍረስ በማሰብ የሸግግር መንግስት ሰነድ ማዘጋጀት ወንጀል ክስ ላይም አቶ ልደቱ አያሌው የጤና ሁኔታቸው አስጊ ደረጃ ላይ መሆናቸውን ገልጸው የሃኪም ማስረጃ በማቅረብ የጠየቁት የዋስትና ጥያቄን መርምሮ ትዕዛዝ ለመስጠት የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምስራቅ ምድብ ችሎት ለህዳር 18 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ ይታወሳል።
 
በታሪክ አዱኛ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.