Fana: At a Speed of Life!

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት 25ኛ አመት የምስረታ በዓሉን ምክንያት በማድረግ 3ኛውን የውይይት መድረክ አካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 25ተኛ አመት የምስረታ በዓሉን በተለያዩ ከንውኖች እያከበረ የሚገኝው ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዛሬ ሶስተኛውን የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ አካሂዷል።
ውይይቱ “ለዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ እና ለሀሳብ ብዝሀነት የሚዲያዎች ሚና” በሚል ርዕስ ነው የተካሄደው።
በመድረኩ በግጭት ወቅት የሚዲያዎች ሚና ምን መምሰል እንደሚኖርበት ምክክር ተደርጎበታል።
በፕሮግራሙ ላይ የዴሞክራሲ ተቋማት የተለያየ ዘርፍ ምሁራን እና የሚዲያ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እያከበረ የሚገኘውን 25ኛ አመት በአል አስመልክቶ ከዚህ ቀደም ባለፉት 25 አመታት በሀገረ መንግስት ግንባታ የሚዲያው ሚና
እና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ የሚዲያ ተደራሸነት እና ስርጭት ዙሪያ ያተኮሩ የውይይት መድረኮችን ማዘጋጀቱ የሚታወስ ነው።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.