Fana: At a Speed of Life!

በሃገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የወጣቶች መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ህዳር 10 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሁሉም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ ወጣቶች የተሳተፉበት በሃገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የወጣቶች መድረክ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በመድረኩ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ “ኢትዮጵያ ደከመች ስትባል የምትጠነክር ሃገር ናት” ብለዋል።

በትግራይ የህወኃት ቡድንን ለህግ ለማቅረብና ህግ ለማስከበር በሚካሄደው ዘመቻ ህዝቡ ለሃገር መከላከያ ሰራዊት እያደረገ ያለው ድጋፍ የዚህ ማሳያ እንደሆነ ጠቅሰዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ወጣቱን በሰላም፣ በኢኮኖሚና በስራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ እንደሆነም ተናግረዋል።

ከሚፈጠረው የስራ ዕድል ወጣቱን 70 በመቶ ያህል ተጠቃሚ ለማድረግ ግብ መቀመጡንም አመልክተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወጣቶችና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብርሃም ታደሰ በበኩላቸው ባደረጉት ገለጻ፤ በከተማዋ ወጣቱን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስራዎች በስፋት እየተከናወኑ ነው።

በህወኃት ላይ እየተወሰደ ያለው ህግ የማስከበር ዘመቻ ላይ ወጣቱ የአካባቢውን ሰላም በማስጠበቅ የበኩሉን መወጣት እንዳለበት ማስገንዘባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.