የዓለም ህፃናት ቀን በሃዋሳ ከተማ ተከበረ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የዓለም ህፃናት ቀን በዓለም ለ31ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ለ15ኛ ጊዜ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሃዋሳ ከተማ ተከበረ፡፡
በዓሉ የተከበረው ትውልድን እንቅረፅ ሃገርን እንገንባ በሚል መሪ ቃል ነው፡፡
የዓለም ህፃናት ቀን በብሔራዊ ደረጃ ከህዳር 9 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በተለያዩ ዝግጅቶች ሲከበር ቆይቷል፡፡
ዛሬ የበዓሉ ማጠቃለያ ፕሮግራም በሃዋሳ ከተማ ሚሊኒየም አዳራሽ መከናወኑን ከሴቶች፣ ህፃናት እና ወጣቶች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡