Fana: At a Speed of Life!

የሐረሪ ክልል የንግድ ማህበረሰብ አባላት ለመከላከያ ሰራዊት ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገቡ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሐረሪ ክልል የንግድ ማህበረሰብ አባላት ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል።

በክልሉ የሚገኙ የንግድ ማህበረሰብ አባላት በሀገራዊ፣ ክልላዊና ወቅታዊ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ከክልሉ ብልጽግና ፓርቲ እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት አካሄደዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በእለቱ ከ10 ሚሊየን ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ ለሀገር መከላከያ ሰራዊቱ ለማድረግ ቃል የገቡ ሲሆን፥ በተጨማሪም ደም በመለገስ፣ የቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ ከሰራዊቱ ጎን ለመሰለፍ ዝግጁ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡

የሐረሪ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አብዱጀባር መሀመድ በውይይት መድረኩ እንደገለጹት፥ ጁንታው የህውሃት ቡድን በተለይም ከለውጡ ወዲህ በተለያዩ በሀገሪቱ አካባቢዎች ሴራዎችን በማሴር በዜጎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሲያደርስ ቆይቷል።

መንግስት በሆደ ሰፊነት በመንቀሳቀስና ችግሩ እንዲቀር ጥረት ቢያደርግም ፅንፈኛው ህውሃት ከድርጊቱ ሊቆጠብ አልቻለም፣ ይባስ ብሎም በሀገር መከላከያ ሰራዊት የሰሜን ዕዝ አባላት ላይ ጥቃት ማድረሱን ገልጸዋል።

መንግስት በሀገሪቱ ሰላም እንዲሰፍንና የዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅ ህግን የማስከበር ስራ እያከናወነ ይገኛል ሲሉም ገልጸዋል።

የንግዱ ማህበሰረብም ከሃገር መከላከያ ሰራዊት ጎን በመሰለፍ ሃገራዊ ሃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ መግለዐፃቸውንም ከሐረሪ ከልል የምንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.