ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ ከጣሊያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ኮንቴ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 15 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የተላከ መልዕክት ለጣሊያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ አቅርበዋል።
በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የሚመራ የመንግሥት ከፍተኛ ልዑክ ዛሬ ሮም ጣሊያን ገብቷል።
ኢትዮጵያ በውስጥ ጉዳይ የጀመረችው ህግ የማስከበር እርምጃ በሃላፊነት እና በጥንቃቄ ሊጠናቀቅ እንደሚችል ያላቸውን ተስፋ የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ ገለፁ።
በውይይቱ ወቅት በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ማብራሪያ የሰጡት አቶ ደመቀ፤ በሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል የተጀመረው ህግ የማስከበር እርምጃ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ መድረሱን አስረድተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በውስጥ ጉዳይ የጀመረችው ህግ የማስከበር እርምጃ በሃላፊነት እና በጥንቃቄ ሊጠናቀቅ እንደሚችል ያላቸውን ተስፋ መግለፃቸውን በሮም ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ሁለቱ ሃገራት ረጅም ዘመን የዘለቀ ጠንካራ ግንኙነት ወደ ተሻለ የትብብር ከፍታ ለማድረስ ጠንክረው እንደሚሰሩ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል።