ዝቅተኛ የደመወዝ መጠንን ለመወሰን የሚያስችል የደመወዝ አወሳሰን ተቋመ እየተደራጀ ነው
አዲስ አበባ፣ታህሳስ 21፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ዝቅተኛ የደሞዝ መጠንን ለመወሰን የሚያስችል የደሞዝ አወሳሰን ተቋመ እያደራጀ መሆኑን የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚነሰቴር ገለጸ።
በሀገሪቱ የአሰሪና ሰራተኛ ሀግ መሰረት የደሞዝ መጠን ለቀጣሪው አና ተቀጣሪው የተተወ ጉዳይ ነው።
ሀጉ ውሳኔውን ለሁለቱ ወገን ቢተወውም በሀገሪቱ ያለው ከፍተኛ የስራ ፈላጊ መጠን እና አነስተኛ የቀጣሪ መጠን በተለያየ መንገድ ሰራተኛው በአሰሪው ተጽዕኖ ስር አንዲወድቅ አድርጎታል።
ከደሞዘ ጋረ የተያያዘው ጉዳይ ሲነሳም ተመሳሳይ ነገር ይስተዋላል።
ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚነስቴር የሰላማዊ ኢንዱስትሪ ልማት ዳይሬክተር አቶ ፍቃዱ ገብሩ፥አሁን ላይ መንግስት ይህን በተቀጣሪ ላይ የሚፈጠረውን ጫና ለመቀነስ የሚያስችል የደሞዝ አወሳሰን ተቋም ለማደራጀት አቅዶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ተናግረዋል።
ተቋሙ የተለያዩ ባለሞያዎችን በቦርድ አባልነት የሚይዝ ሲሆን፥በየጊዜው የተለያዩ ጥናቶችን በማጥናት የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ ያስገባ ዝቅተኛ የደሞዝ መስፈርት ያስቀምጣል።
ውሳኔውም ነሀሴ 30 የጸደቀው የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ደንብ ቁጥር 156/ 2011 ዝቅተኛ የደሞዝ መጠንን በማቅረብ በመንግስት የሚያስወስን ቦርድ እንዲቋቋም በሰጠው ድጋፍ መሰረት የተከናወነ ነው።
ወቅታዊ የሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴም ይህን ለማድረግ እንዳስገደደ ነው አቶ ፈቃዱ የገለጹት።
ይሁን እንጂ ቦርዱ ይህን በጥናት የተደገፈ ዝቅተኛ የደሞዝ መጠንን ቢያቀርብም፥በቀጣሪው ላይ ይህን ያህል ደሞዝ ክፈል የሚል ጫናም ሆነ ግፊት አያደርግም።
በአንፃሩ በቦርዱ ውስጥ ያሉት ሰራተኞች ወቅታዊ የሀገሪቱን እና የሰዎችን የኑሮ ሁኔታ ግምት ውስጥ ያስገባ ዝቅተኛ የደሞዝ መጠን እንዲኖር በመሃል ሆነው የአደራዳሪነት ሚናን ይጫወታሉ።
ድርድሩ ቀጣሪው ምርታማ ሆኖ በስራው የመቆየት አቅምንም ግምት ውስጥ የሚያስገባ መሆኑም ተመላክቷል።
በአሁኑ ወቅትም ይህን ቦርድ ለማቋቋም የሚያስችለው ደምብ እየተዘጋጀ ነው ያሉት አቶ ፈቃዱ ፥አለም አቀፍ ተሞክሮዎች እና ልምዶች እየተካተቱበት መሆኑም አንስተዋል።
የማቋቋሚያ ደምቡን እስከ ግንቦት ወር አጠናቆ ለምክር ቤት የማቅረብ እና ስራውበፈረንጆቹ አዲስ አመት 2020 የመጀመር እቅድ መኖሩንም ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።
በትዕግስት አብርሃም