Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን ከተመድ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 22፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የወጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛ ፓርፋይት ኦናንጋ ጋር ተወያዩ።

በውይይቱ ወቅትም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የወጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፥ መንግስት በትግራይ ክልል ባካሄደው ህግን የማስከበር ዘመቻ ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በዘመቻው በንጹሃን ዜጎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ከፍተኛ ጥንቃቄ ስለመደረጉም አብራርተዋል።

የፌደራሉ መንግስት ክልሉን መቆጣጠሩን እና ነፃ በወጡ አካባቢዎችም ጊዜያዊ አስተዳደር ማቋቋም መጀመሩንም አብራርተዋል።

እንዲሁም ነፃ በወጡ አካባቢዎች መንግስት ሰብአዊ ድጋፎችን ማቅረብ መጀመሩንም እና ድጋፉም በመንግስት አካላት በተካሄደ የዳሰሳ ጥናት መሰረት ቅድሚያ ለሚያስፈልጋቸው አካባቢዎች እንዲደረስ እየተደረገ ነውም ብለዋል።

ግጭቱን ሸሽተው ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ በመንግስት በኩል ያለውን ዝግጁነትም አብራርተዋል።

የተመድ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛ ፓርፋይት ኦናንጋ በበኩላቸው ስለተደረገላቸው ገለፃ አመስግነው፤  ለተጎዱ አካባቢዎች የሚደርስ የሰብአዊ ድጋፎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።

እንዲሁም ንፁሃን ዜጎች እንይጎዱ የሚደረገው ጥንቃቄ ተጠናክሮ አንዲቀጥል እንዲሁም የሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩም መጠየቃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴረ መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.