Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን በ21ኛው አፍሪካ ሕብረት ልዩ የሥራ አስፈፃሚዎች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ተካፈሉ

አዲስ አበባ ፣ህዳር 23 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን በቪዲዮ ኮንፈረንስ በተካሄደው በ21ኛው አፍሪካ ሕብረት ልዩ የሥራ አስፈፃሚዎች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ተካፍለዋል።

ስብሰባው በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጠና ትግበራ እና በ2020 የአፍሪካ ህብረት ዓመታዊ መሪ ቃል ”ጠመንጃዎችን ማዘጋት” የትግበራ ሁኔታ ላይ ትኩረት ያደረገ ነበር ፡፡

አቶ ደመቀ መኮንን በስበብሰባው ላይ ባስተላለፉት መልእክትም የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ለአፍሪካ አህጉራዊ አጀንዳዎች ጠቀሜታ እንዳለው ጠቁመው÷ በተለይም የአፍሪካን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማትና ውህደት ለማሳደግ ያስችላል ብለዋል ፡፡

አያይዘውም ኢትዮጵያ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጠና ስምምነት ላይ የነበራትን ተሳትፎ አስታውሰው ÷ የስምምነቱን ድንጋጌዎች ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ ያላትን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል ፡፡

ከዚህ ባለፈም የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና ደህንነት ምክር ቤት አባል እንደመሆኗ በ2020 የስራ ዘመን መሪ ቃሉን በመተግበር ለተገኙት አዎንታዊ ውጤቶች ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክታለች ብለዋል ሚኒስትሩ፡፡

በዚህ ስብሰባም ምክር ቤቱ በታህሳስ 5 እና 6 ቀን የሚካሄደውን የአፍሪካ ህብረት 13ኛ እና 14ኛ ልዩ ስብሰባ የቀረቡትን ረቂቅ አጀንዳዎችና ውሳኔዎችን መመልከቱን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.