Fana: At a Speed of Life!

በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ በ70 ሚሊየን ዩሮ ካፒታል ወደ ስራ የገባው የሶፍሌት ማልት ኢትዮጵያ መጋቢት ወር ላይ ምርት ይጀምራል

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 25፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ በ70 ሚሊየን ዩሮ ኢንቨስትመንት ካፒታል ወደ ስራ የገባው የሶፍሌት ማልት ኢትዮጵያ ፋብሪካ መጋቢት ወር ላይ ምርት ይጀምራል ተባለ፡፡
ፋብሪካው በፈረንሳይ ቀዳሚ የጥራጥሬ ሰብሳቢ ሲሆን በ70 ሚሊየን ዩሮ ኢንቨስትመንት ካፒታል ወደ ስራ ገብቷል፡፡
ተቋሙ በ10 ሄክታር ላይ የሚያርፍ የብቅል ፋብሪካ እየገነባ ሲሆን ከጅምሩ ከ25 ሺህ አርሶ አደሮች ጋር የምርት ትስስር ፈጥሮ እየሰራ ይገኛል፡፡
በሙሉ አቅሙ ስራ ሲጀምርም ትስስሩን ወደ 40 ሺህ ለማሳደግ አቅዶ እየሰራ እንደሚገኝ ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡
ሙሉ በሙሉ የሀገር ውስጥ የግብርና ምርትን ተጠቅሞ ከ100 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ ብቅል በአመት የማምረት አቅም ያለው ይህ ፋብሪካ በመጋቢት ወር 2013 ዓ.ም ወር ምርት ይጀምራል ተብሏል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.