Fana: At a Speed of Life!

በአውሮፓ የሚሰሩ ትውልደ አትዮጵያውያን እና ኢትዮጵያውያን ምሁራን ለአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ፕሬዚዳንት ዴቪድ ሳሶሉ ደብዳቤ አስገቡ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአውሮፓ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እና ኩባንያዎች የሚሰሩ ትውልደ አትዮጵያውያን እና ኢትዮጵያውያን ምሁራን በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ፕሬዚዳንት ዴቪድ ሳሶሉ ደብዳቤ አስገቡ፡፡
ምሁራኑ እና ባለሙያዎቹ በደብዳቤያቸው ጽንፈኛው የህወሓት ቡድን የፈጸመውን ጥቃትና ህገ ወጥ ድርጊት የተመለከተ ማብራሪያ ጽፈዋል፡፡
ለፕሬዚዳንቱ በተለያዩ ሃገራት የሚኖሩ 22 የሚደርሱ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና ኢትዮጵያውያን ምሁራን እና ባለሙያዎች በደብዳቤያቸው መንግስት በትግራይ ክልል ስላከናወነው ህግ የማስከበር ዘመቻ በተመለከተ ገልጸዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም አሁን ላይ የሃገር ክህደት የፈጸሙ የጽንፈኛው ህወሓት ቡድን አባላትን ለህግ የማቅረብ ስራ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
በደብዳቤያቸውም ኢትዮጵያ ምርጫ ለማካሄድ እንቅስቃሴ መጀመሯን ጠቅሰው ከአሁን በፊት ሊካሄድ ታስቦ የነበረው ምርጫ በኮቪድ19 ምክንያት መራዘሙን አስታውሰዋል፡፡
በጀርመኑ መርቼዲስ ኩባንያ የሚሰሩት ዶክተር ፀጋዬ ደግነህ፣ የኔዘርላንድሱ ዶክተር አያሌው ካሳሁን፣ ዶክተር ዘሪሁን አሰፋ ከቤልጂየም፣ ፕሮፌሰር አስናቀች ስዩም ከጀርመን፣ ዶክተር ኮንቴ ሙሳ ከስዊድን፣ ዶክተር ዘላለም ኤሪሶ ከጣልያን፣ልዑል አስፋውወሰን አስራተ ካሳ፣ ፕሮፌሰር በላቸው ገብረወልድ ከስዊዘርላንድን ጨምሮ 22 የሚደርሱና በተለያዩ ሃጋራት የሚሰሩ ምሁራን እና ባለሙያዎች ናቸው ደብዳቤውን ያስገቡት፡፡
ስላባት ማናዬ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.