Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከካናዳ የፓርላማ አባላት እና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ሃላፊዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በካናዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ከካናዳ የፓርላማ አባላት ፣ መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ሃላፊዎች ፣ኢትዮ ካናዳዊያን ኔትወርክ ለማህበራ ድጋፍ ስራ አስፈጻሚ አባላትናሌሎች ተሳታፊዎች በተገኙበት በዌብናር ውይይት አካሂደዋል።
በውይይቱም ኢትዮጵያ በተለይ ከለውጡ ቀደም ብሎ በአገሪቱ የተቀጣጠለውን ህዝባዊ አመፅና ይህንኑ ተከትሎ በአገሪቱ ለውጥ መምጣቱን ገልጸዋል።
ለውጡን ተከትሎም መንግስት አገሪቱን ለማረጋጋትና የህዝብ ጥያቄን ለመመለስ መንግስት የፖለቲካ እስረኞች መፍታት፣ የፖለቲካ ምህዳር የማስፋት፣ አሳሪ የሆኑ የህግ ማእቀፎችን የማሻሻል፣ ምርጫ ቦርድን እንደገና ገለልተኛ ሆኖ እንዲዋቀርና በገለልተኛ ሰው እንዲመራ የማድረግ፣ የተለያዩ የኢኮኖሚ ማሻሻያ እርምጃዎች መወሰዳቸውን ጨምረው አስረድተዋል፡፡
አምባሳደሯ አያይዘውም ይህ ሁሉ ሲሆን ጽንፌኛው የህወሃት ቡድን በአገሪቱ ሰላምና መረጋጋት እንዳይኖርና በለውጡ ያጣውን ስልጣን መልሶ ለመያዝ እንዲቻለው በማሰብ በመሸገበት ሆኖ የተለያዩ ቡድኖችን በመመልመል፣ በማደራጀት፣ በማሰልጠንና ገንዘብና ሚሽን ሰጥቶ በማሰማራት ብሔርን ከብሔር እንዲሁም ሃይማኖትን ከሃይማኖት ለማጋጨት ከፍተኛ እኩይ ተግባር ላይ ተሰማርተው ሲሰሩ የነበሩ እና በመጨረሻም በስሜን ዕዝ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ ጥቃት መፈፀማቸውን አብራርተዋል።
ጽንፈኛው የህወሃት ቡድን በሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ የፈፀመውን ክህደት ተከትሎ መንግስት የሀገሪቱን ህገመንግስት ለማስከበርና አጥፊዎችን ለህግ ለማቅረብ እየወሰደ ያለውን እርምጃ በዝርዝር አስረድተዋል፡፡
ከዚህ እርምጃ ቀደም ብሎም መንግስት ጉዳዩን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ሁሉንም አማራጮች ተጠቅሞ ያደረውን ጥረትና ቡድኑ እምቢተኛ በመሆኑ አለመሳካቱን ጨምረው ገልጸዋል ።
መንግስት የወሰደውን እርምጃ ተከትሎ ትግራይ ክልል መቀሌን ጨምሮ በመንግስት ቁጥጥር ስር መሆኑና ወንጀለኞቹን ለህግ የማቅረብ ስራ እየተካሄደ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡
የፓርላማ አባላቱም የተሰጣቸው ገለፃና ማብራሪያ ሁኔታውን በደንብ እንዲረዱ እንዳደረጋቸው ጠቁመው÷ በህግ ማስከበሩ ሂደት ሰብዓዊ ቀውሶችን ለመቀነስ ትኩረት መስጠት ያለበት መሆኑንና በካናዳ በኩል አስፈላጊው ድጋፍ ሲኖር እንዲገለፅላቸው ጠይቀዋል።
ኢትዮጵያ ከካናዳ ብዙ የምትወስዳቸው ልምዶች መኖራቸውና ለአብነትም በመልሶ ማቋቋም፣ ብሔራዊ መግባባትን ከማስፈንና በቀጣይ ምርጫም ልምድ የማካፈል ጋር ተያይዞ ካናዳ ማገዝ የምትችልባቸው መስኮች መሆናቸው እንደተገለጸላቸው በካናዳ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.