ከማዕድን ዘርፍ ባለፉት 4 ወራት 269 ነጥብ 1 ሚሊየን ዶላር ገቢ ተገኘ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 27፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከማዕድን ዘርፍ ባለፉት አራት ወራት 269 ነጥብ 1 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ መገኘቱን የማዕድን እና ነዳጅ ሚኒስቴር አስታውቋል።
በአራት ወር ውስጥ ከ3 ሺህ 600 ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ ለውጪ ገበያ መቅረቡንም ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው።
የማዕድን እና ነዳጅ ሚኒስትር ኢንጂር ታከለ ኡማ በማዕድን ዘርፍ አፈፃፀምና ቀጣይ እቅዶች ዙሪያ ከክልል የማዕድን ቢሮ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አድርገዋል።
ኢንጂነር ታከለ ኡማ እንደተናገሩት መንግስት ለዘርፉ ትኩረት ሠጥቶ እየሰራ ሲሆን፥ ባለፉት አራት ወራት 3 ሺህ 602 ኪሎ ግራም ወርቅ ለውጭ ገበያ ቀርቦ 265 ነጥብ 8 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ተገኝቷል።
ከጌጣጌጥ ማዕድናት ደግሞ 3 ነጥብ 215 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ መገኘቱንም አስታውቀዋል።
በእቅድነት የተያዘው የወርቅ ምርት የተከለሰ ሲሆን፥ በተሻለ መንገድ ኢኮኖሚውን መደገፍ በሚያስችል መልኩ ምርቱን ለመጨመር ከክልል አመራሮቹ ጋር መግባባት ላይ መደረሱንም ሚኒስቴሩ ያወጣው መረጃ ያመለክታል።
በቀጣይም ዘርፉን ዘመናዊ መልክ ለማስያዝ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ተገልጿል።
የማዕድን ፈቃድ ተሰጥቷቸው በአግባቡ እየተጠቀሙበት ያልሆኑ ተቋማት ላይ መወሰድ ስላለበት እርምጃ በተመለከተ ውይይት ተደርጓል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!