Fana: At a Speed of Life!

ኢንጂነር አይሻ ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 30፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር  ኢንጂነር አይሻ መሀመድ ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ፡፡

ውይይቱ ተቋማቱ በጋራ አብሮ መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ ማተኮራቸው ነው የተገለጸው፡፡

ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ጋር በተያያዘ የሚከናወኑ የመሰረተ ልማት፣ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ጋር በተያያዘ የሚከናወኑ የስፓሻል ፕላን ስራዎች እንዲሁም ከተሞች ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ተጠቃሚ በመሆንና ገቢያቸውን ማሳደግ ስለሚችሉባቸው ጉዳዮች የጋራ ምክክር መደረጉን ነው የተጠቀሰው፡፡

ኢንጂነር አይሻ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የዘርፉን የ10 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድበተለያየ ደረጃ በማወያየትና በማዳበር ወደትግበራ ለመግባት በዝግጅት ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

በተለይም የመኖሪያ ቤቶችን ጉዳይ ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ ለመስራት በሚያስችል ደረጃ መታቀዱንም ነው ያነሱት፡፡

መንግስት የመኖሪያ ቤቶችን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የተለያዩ አማራጮች ማስቀመጡንም ጠቅሰዋል፡፡

ለዚህም ትልቅ መደላድል በመፍጠር የሚታዩ ችግሮችን መልክ እንደሚያስይዝ የሚታመነው የመኖሪያ ቤቶች ልማትና ግብይት አዋጅ በቅርቡ ይፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ነው ያስረዱት፡

የኮርፖሬሽኑ የሥራ ኃላፊዎች በበኩላቸው የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት የሚጠበቀውን ውጤት እንዲያመጣ በብዙ ዘርፎች ላይ ከሚኒስቴሩ ጋር በቅንጅት ለመስራት እንደሚፈልጉ ተናግረዋል፡፡

በቀጣይም ሁለቱ ተቋማት በጋራ አብሮ ለመስራት የሚቻልባቸውን አቅጣጫዎች ማስቀመጣቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

 

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል

https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.