ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረትና የተመድ ድንጋጌዎችን አክብራ ትሰራለች – አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 2፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ድንጋጌዎችን አክብራ ትሰራለች አሉ በተመድ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ፡፡
አምባሳደሩ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሙስናን ለመከላከል ያፀደቃቸውን ድንጋጌዎችና ስምምነቶችን አክብራ እየሰራች መሆኑን አብራርተዋል፡፡
በአፍሪካ ግጭቶችን ማስቀረት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ የንቅናቄ መፍጠሪያ ውይይት ተካሂዷል፡፡
ውይይቱ ላይ በሰጡት ሀሳብ ኢትዮጵያ አህጉራዊ እና አለማቀፋዊ ድንጋጌዎችን አክብራ እየሰራች መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በአፍሪካ በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ምክንያት ግጭትና ያለመረጋጋት እንዳይፈጠር በትብብር መስራት ያሻል ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ ራስ ወዳድ እና ወንጀለኛ ቡድኖች የህዝብና የሀገር ጥቅምን ወደ ጎን በመተው ችግር ለመፍጠር የሚንቀሳቀሱ እንዳሉ ጠቅሰዋል፡፡
ሆኖም የሕግ የበላይነትን በማስከበር ነገሮች ስርዓት እንዲይዙ ይደረጋል ነው ያሉት፡፡
በአጠቃላይ ችግሩን ለመፍታት በትብብር በመስራት ህገወጥ የገንዘብ ዝውውርን መግታት እና የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል፡፡
በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ድንጋጌዎችን አክብራ ለማስከበርና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሁሉ በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆኗን አሳውቀዋል፡፡
በቪዲዮ ኮንፍረንስ በተካሄደው ውይይት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባል ሀገራት፣ የአፍሪካ ህብረት፣ አጋር ድርጅቶች፣ ሲቪል ማህበረሰብ እና የምሁራን ተወካዮች ተሳትፈዋል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!