Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ገለልተኛ የብሄራዊ የኢኮኖሚ ምክር ቤት ተመሰረተ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 5 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ገለልተኛ የብሄራዊ የኢኮኖሚ ምክር ቤት መመስረቱን  የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት አስታውቋል።

የመንግሥትን የማሻሻያ ፕሮግራም በስኬት ለማስፈጸምና በአጠቃላይ የኢኮኖሚውን እድገት ቀጣይነት ለማረጋገጥ የምሁራንና የባለሙያዎችን ምክር እንዲሁም ግብረ መልስ መቀበል ጠቃሚ መሆኑን ነው ፅህፈት ቤቱ የገለፀው።

ገለልተኛ ከሆኑ ምሁራንና ባለሙያዎች ሃሳብ መቀበል የፖሊሲን አካታችነት ከመጨመር ባለፈ፤ ያልታዩ ጉዳዮችን ለማየት፣ ሃገሪቱ ያለችበትን ውስብስብ የሆነ የድህነትንና ሌሎች ማኅበራዊ ችግሮችን ለመረዳትና ውጤታማ የፖሊሲ አማራጮችን ለመመርመር ያስችላል ነው የተባለው።

ከዚህ በመነሳትም በታህሳስ 21 ቀን 2012 ዓ.ም. በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በወጣው ማስታወቂያ መሰረት የገለልተኛ ብሔራዊ የኢኮኖሚ ምክር ቤት እጩ አባላትን በጥቆማና በስራ ማመልከቻ መቀበል መጀመሩን ይፋ አድርጎ እንደነበር ነው ፅህፈት ቤቱ የገለፀው።

ይህንን ጥሪ ተከትሎም በጥቅሉ ወደ 290 እጩዎች የቀረቡ ሲሆን፣ በሶስት ደረጃ የተከፈለ የማጣራት ሂደት ከተከናወነ በኋላ 16 ምሁራን ፍቃደኝነትታቸው ተረጋግጦ የመጀመሪያው የገለልተኛ ብሔራዊ የኢኮኖሚ ምክር ቤት አባላት ሆነው መመረጣቸው ተጠቁሟል።

በዚህም መሰረት÷

  1. ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ
  2. ፕሮፌሰር ብርሃኑ አበጋዝ
  1. ፕሮፌሰር ጋቢሳ እጀታ
  2. ፕሮፌሰር መላኩ ደስታ
  3. ፕሮፌሰር ሰይድ ሀሰን
  4. ዶክተር ታደለ ፈረደ
  5. ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና
  6. ዶክተር አለማየሁ ስዩም
  7. ዶክተር አሉላ ፓንክረስት
  8. ዶክተር ዲማ ነገዎ
  9. ዶክተር እሌኒ ገብረመድህን
  10. ፕሮፌሰር ለማ ወልደሰንበት
  11. ዶክተር ራሄል ካሳሁን
  12. ዶክተር ሰገነት ቀለሙ
  13. ዶክተር ዮናስ ብሩ
  14. አቶ ህላዊ ታደሰ የገለልተኛ የብሔራዊ የኢኮኖሚ ምክር ቤት አባላት ሆነው ተመርጠዋል።

 

 

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.