Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል የተወሰደው ህግን የማስከበር እርምጃ  በመተከል ዞንም እንዲደገም ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በትግራይ ክልል የተወሰደው ህግን የማስከበር እርምጃ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞንም እንዲደገም ተጠየቀ።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ብልጽግና ፓርቲ የሴቶች ሊግ አባላት በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ በአሶሳ ከተማ ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ ጁንታው የመተከልን የአስተዳደር መዋቅር በማፈራረስ በራሱ ቡድን ለመተካት ጥረት አድርጓል ብለዋል፡፡

የህወሓት ኢ-ህገ መንግስታዊ ተግባር በጤናማ አዕምሮ የማይታሰብ ነው ያሉት የውይይቱ ተሳታፊች÷ የጥፋት ድርጊቱን አውግዘዋል፡፡

በመተከል እየተፈጸመ የሚገኘው ግፍ በትግራይ ክልል በቅርቡ ከሆነው ጥፋት የማይተናነስ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

ህወሓት በመተከል ባደረሰው ጥፋት ዋነኛ ተጠቂዎች ሴቶች እና ህጻናት እንደሆኑ በመጥቀስም ችግሩ በፍጥነት መቆም እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡

የጥፋት ቡድኑ አመራሮችም በአስቸኳይ ለፍርድ መቅረብ እንዳለባቸው አመልክተው በትግራይ ክልል የተወሰደው ህግን የማስከበር እርምጃ በመተከልም እንዲደገም መጠየቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.