አምባሳደር ነብያት የህግ ማስከበር ዘመቻው መጠናቀቁን ገለጻ አደረጉ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአልጄሪያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው በትግራይ ክልል የተወሰደው ህግ የማስከበር ዘመቻ በስኬት መጠናቁን ገለጹ፡፡
አምባሳደር ነብያት ከአልጀሪያው ኤል ቻብ ጋዜጣ ጋር በትግራይ ክልል ከተወሰደው የህግ ማስከበር ዘመቻ እና ሃገራዊ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ቆይታ አድርገዋል፡፡
በቆይታቸውም በአሁኑ ወቅት ወንጀለኞችን የማደንና የመልሶ ግንባታ ስራ እየተካሄደ መሆኑን ነው ያስረዱት፡፡
ከዚህ ባለፈም በህግ ማስከበር ዘመቻው የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀያቸው የመመለስ ስራ እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
እንዲሁም ኢትዮጵያና አልጄሪያ ከመሰረቱት ጠንካራ የፖለቲካ ግንኙነት ባሻገር በኢኮኖሚው ዘርፍ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር እምቅ አቅም አላቸው ብለዋል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!