Fana: At a Speed of Life!

በሱማሌ ክልል በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ9 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሱማሌ ክልል ሲቲ ዞን በህገ-ወጥ መንገድ ሰዎችን ጭኖ ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲጓዝ በነበረ የሚኒባስ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የዘጠኝ ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ23 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት ደረሰ::
አደጋው የደረሰው ትላንት ከለሊት 9 ከ30 ገደማ በሱማሌ ክልል ሲቲ ዞን ከለበዴ ቀበሌ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ወደ ጅቡቲ በሚወስደው ፈጣን መንገድ ላይ የሚኒባስ ተሽከርካሪ 32 ሰዎችን በህገወጥ መንገድ ወደ ጂቡቲ ለማሻገር ጭኖ ሲጓዝ በተጠቀሰው ስፍራ የኋላ ጎማው በመፈንዳቱና ተሽከርካሪው በመገልበጡ ነው፡፡
በዚህም ሹፌሩን ጨምሮ የዘጠኝ ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ በ23 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል::
ጉዳት የደረሰባቸው ተጎጂዎች በድሬደዋ ድል ጮራ ሪፈራል ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ከድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.