Fana: At a Speed of Life!

የኢጋድ 38ኛው አስቸኳይ የመሪዎች ጉባኤ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) 38ኛው አስቸኳይ ጉባኤ በጅቡቲ ተካሄደ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የሱዳን ፣ የኬንያ ፣ የሶማሊያ ፣ የጅቡቲ እና የደቡብ ሱዳን መሪዎች ተሳትፈዋል፡፡

በስብሰባው የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ መሀመት እና የኢጋድ ዋና ፀሃፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁም ተሳታፊዎች ናቸው፡፡

የወቅቱ የኢጋድ ሊቀመንበር የሱዳኑ ፕሬዚዳንት አብደላ ሃምዶክ የኢጋድ አባል ሀገራት ኮቪድ 19 ፣ የአንበጣ መንጋ ወረረርሽኝ የተቆጠጠሩበትን መንገድ እና በደቡብ ሱዳን ያለውን ፈጣን የዴሞክራሲ ሽግግር አድንቀዋል።

አብደላ ሀምዶክ በበርካታ ጉዳዮች ዘላቂ ምላሽ ለመስጠት መሪዎቹ ያላቸው የወንድማማችነት መንፈስ የሚደነቅ እንደሆነም ተናግረዋል።

ይህ ስብሰባ በቀጠናው በአሁን ወቅት አስቸኳይ ምላሽ ለሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች አስፈላጊውን አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥ ገልፀዋል።

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሀመት በበኩላቸው የኢትዮጵያ መንግስት የሀገርን አንድነት ለማስጠበቅ የሄደበትን ጠንካራ መንገድ አድንቀው ህግን በማስከበር እርምጃው ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች ለማቋቋም ቀጣይነት ያለው ጥረት ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.