Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ዓለምፀሃይ ከኡጋንዳ የፀጥታ ሚኒስትር ጋር በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 13 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኡጋንዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዓለምፀሃይ መሰረት ከሃገሪቱ የፀጥታ ሚኒስትር ጋር በወቅታዊ ሁኔታ ላይ ውይይት አደረጉ።
አምባሳደር ዓለምፀሃይ በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳዮች፣ በትግራይ ክልል ስለተካሄደው የህግ ማስከበር እና መልሶ ማቋቋም እርምጃ ለደህንነት ሚኒስትሩ ገለፃ አድርገውላቸዋል።
በውይይቱ ወቅት የህግ-ማስከበር ዘመቻው ከመነሻው በተቀመጠለት አላማ እና የጊዜ ገደብ በስኬት የተጠናቀቀ መሆኑን አምባሳደሯ ገልጸዋል።
በዘመቻው ጊዜም የጎረቤት ሀገራት ጉዳዩ የኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ መሆኑን በመረዳት የውጭ ጣልቃ ገብነትን ለመከላከል ያደረጉት ድጋፍ ከፍተኛ እንደነበር ገልፀውላቸዋል።
አያይዘውም በአሁኑ ወቅት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከመንግስት ጋር በመሆን ክልሉን በአጭር ጊዜ መልሶ ለማቋቋም እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል።
አምባሳደር ዓለምፀሃይ አክለውም የተበተኑ ወንጀለኞችን ወደ ህግ የማቅረቡ ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉንም አንስተዋል።
የዩጋንዳ የፀጥታ ሚኒስትር በበኩላቸው÷ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተሉት እንደሆነና መንግስት ህግን ለማስከበር እያደረገ ያለውን ጥንቃቄ የተሞላበት እርምጃ እንደሚያደንቁ ተናግረዋል።
ሚኒስትሩ አያይዘውም ሁለቱ ሀገራት ረጅምና ጠንካራ ግንኙነት ያላቸው ወዳጅ ሀገራት እንደመሆናቸው በዚህ ወቅትም መተባበር አስፈላጊ መሆኑን አውስተዋል።
በዚህም ኡጋንዳ በህግ-ማስከበሩ ሂደት እንደወዳጅ ሀገር ለመተባበር ዝግጁ መሆኗን መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.