Fana: At a Speed of Life!

ወደ ትምህርት ቤት እንመለስ በሚል ንቅናቄ ሊጀመር ነው

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ወደ ትምህርት ቤት እንመለስ የሚል ንቅናቄ ከነገ ጀምሮ እንደሚካሄድ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ሚኒስቴሩ ከትምህርት ቤት የቀሩ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት በሚመለሱበት ሁኔታ ላይ ከመንግስት ከፍተኛ አመራሮች ጋር በበይነመረብ ውይይት አካሄዷል፡፡
በውይይቱም የጤና ሚኒስቴር፣ የሴቶች እና ህፃናት ሚኒስቴር፣ የግብርና ሚኒስቴር፣ የሁሉም ክልል የብልፅግና ከፍተኛ አመራሮች እና የክልል ቢሮ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል።
በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ ከዘጠኝ ወራት በኋላ ትምህርት ቤቶች ዳግም ወደ መማር ማስተማር ሂደት ቢገቡም ተማሪዎች የሚጠበቀውን ያህል በትምህርት ገበታቸው ላይ አለመገኘታቸው ተገልጿል፡፡
የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ ከነገ ጀምሮ ” ወደ ትምህርት ቤት እንመለስ” የሚል ንቅናቄ የሚጀመር መሆኑንና ሁሉም የሴክተር መስሪያ ቤቶች በንቅናቄው ላይ እንደሚሳተፉ ገልፀዋል።
ንቅናቄውም ለተከታታይ አምስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን ÷ከትምህርት ቤት የቀሩ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እንዲመለሱ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
በንቅናቄውም ቤት ለቤት በመዞር በየቤታቸው የቀሩ ተማሪዎች ከሰኞ ጀምሮ ወደ ትምህርት ቤት እንዲመለሱ ለማድረግ ይሰራል ነው የተባለው።
ምዝገባ ሳያደርጉ የቆዩ ተማሪዎችም እስከ ታህሳስ 23 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ምዝገባ በማድረግ ወደ ትምህርት ቤት እንዲመለሱ እንደሚደረግ ተነግሯል።
የትምህርት ሚኒስትሩ የሴክተር መስሪያ ቤቶች ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ቤት ለመመለሰሰ በሚደረገው ጥረት በየሴክተሩ የበኩላቸውን እንዲወጡም መጠየቃቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.