Fana: At a Speed of Life!

የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ከልሳን ቴክኖሎጂ ጋራ በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ከልሳን ቴክኖሎጂ ጋራ በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ፡፡
ስምምነቱ በሁለቱም ተቋማት ያሉ ተመራማሪዎችን በማስተባበር የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ ውጤት እንደሚያስገኝ የታመነበት መሆኑ ታውቋል፡፡
ስምምነቱን የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን ቀሬ እና የልሳን ቴክኖሎጂን ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ አዳም ቦዶዊን ተፈራርመዋል፡፡
ስምምነቱ ሁለቱ አካላት በቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ እንዲሁም በሁለቱም ተቋማት የሚገኙ ተመራማሪዎች፣ ሶፍትዌር መሀንዲሶች እና ሌሎች ባለሙያዎች በጋራ እንዲሰሩ የሚያደርግ መሆኑን ታውቋል፡፡
በዚህም ልሳን የስልጠና እንዲሁም የማሽን ትራንስሌሽን እና ኦፕቲካል ካራክተር ሪኮግኒሽን ሲስተሞች ድጋፍ የሚያደርግ ሲሆን ኢንስቲትዩቱም ለጋራ ምርምር የሚያስፈልግ መሰረተልማት፣ ቁሳቁስ እና አስተዳደራዊ አቅርቦቶችን የሚያከናውን ይሆናል፡፡
በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን ቀሬ እንዳሉት ÷ኢንስቲትዩቱ በኢትዮጵያ ውስጥ በስልጠና፣ ጥናት እና ቢዝነስ መካከል ድልድይ መሆኑንና በሀገሪቱ ስትራቴጂዎች ውስጥም ቁልፍ ሚና እንደሚጫወት አውስተው ስምምነቱ በፍጥነት ወደ ተግባር እንዲለወጥ ያላቸውን ፍላጎት መግለፃቸውን ከቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.