Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና ዓለም ባንክ የ100 ሚሊየን ዶላር የብድር ስምምነት ተፈራረሙ 

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና የዓለም ባንክ 100 ሚሊየን ዶላር የብድር ስምምነት ተፈራረሙ።

የብድር ስምምነቱ  በጥቃቅንና አነስተኛ ስራ ዘርፍ ለተሰማሩ ሴት ስራ ፈጣሪዎች የሚውል ነው ተብሏል።

የስምምነት ፊርማውን የገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታ ያስሚን ወሀብሬቢ እና በኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳንና ኤርትራ የዓለም ባንክ ዳይሬክተር ኦስማን ዲዮን ናቸው።

ፕሮጀክቱ የገንዘብ እጥረት ያለባቸውን ጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅቶች ብድር የሚያገኙበትን መንገድ ለማመቻቸት እና የኮቪድ ወረርሽኝ ስራቸው ላይ ጉዳት ላደረሰባቸው ሴቶች የሚውል መሆኑንም ሚኒስትር ዲኤታዋ ተናግረዋል።

እንዲሁም ጥቃቅን እና አነስተኛ ድርጅቶችን ለሚመሩ ሴቶች የንግድ ስራ ክህሎት ስልጠና እንደሚያገኙም ገልጸዋል።

በተጨማሪም ለቴክኒክና ሙያ ተቋሟትና ለጥቃቅን አነስተኛ ንግድ ቢሮዎች የቴክኒክ ድጋፍ ለማድረግ ይውላልም ነው የተባለው፡፡

ለመጀመሪያ ጊዜ የብድር አገልግሎት የሚያገኙ ተጠቃሚዎች ያለ ከፍተኛ ማስያዣ ብድር ማግኘት የሚችሉባቸው መንገዶች መመቻቸቱም በዚህ ወቅት ተገልጿል።

የዓለም ባንክ በአጭር ጊዜ ውስጥ ምላሽ በመስጠቱም ሚኒስትር ዲኤታዋ አመስግነዋል፡፡

በቅድስት ብርሃኑ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.