Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ  ክልል በፍትህ  ዘርፍ  ላይ በሚታዩ ተግዳሮቶች  ዙሪያ ከክልሉ የተለያዩ ዞኖች ከተውጣጡ የፍትህ  አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ  ሰብዓዊ መብቶች  ኮሚሽን በኦሮሚያ  ክልል በፍትህ  ዘርፍ  ላይ በሚታዩ ተግዳሮቶች ዙሪያ በክልሉ ከሚገኙ ዞኖች  ከተውጣጡ የፍትህ  አካላት ጋር ውይይት አደረገ::

በመድረኩ ላይ  ከ13 የክልሉ ዞኖች የተውጣጡ  የከፍተኛ ፍርድ  ቤት ፕሬዚዳንቶች፣  የፖሊስ  መምሪያ  ሀላፊዎች  እና የዞን የዐቃቤ  ህግ  ጽህፈት ቤት ሀላፊዎች ተሳትፈዋል።

በዚህ ወቅትም በፍትህ ዘርፉ ላይ የሚታዩ ተግዳሮቶችን የሚዳስስ የውይይት መነሻ  ጽሁፍ  በባለሙያ  ቀርቦ  ውይይት  ተደርጎበታል፡፡

ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ የሚፈፀም እስር ፣ የተራዘመ የቅድመ ክስ እስር፣ በተጠርጣሪዎች ላይ የሚፈፀም ድብደባ፣ የፍርድ  ቤት ትዕዛዝን አለማክበር ፣ በዳኞች ላይ የሚፈፀም ወከባ እና የፍርድ ቤት ነፃነትን በዋናነት የዳሰሰ መሆኑን ከኢትዮጵያ  ሰብዓዊ  መብቶች  ኮሚሽን  ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በፍትህ ዘርፉ ላይ ለሚስተዋሉ  ክፍተቶች አንዳንድ ተሳታፊዎች በክልሉ የሚታየውን የፀጥታችግር በምክንያትነት አንስተዋል።

የህግ የበላይነትን ለማስከበር የሚሰሩ ስራዎች ህግን ያከበሩ መሆን እንዳባቸው እና በየደረጃው ያለው አመራርም ችግሮቹን በቅርበት ክትትል በማድረግ መፍትሄ እየሰጠ መሄድ እንዳለበት ሀሳብ ተነስቷል፡፡

በቀጣይ ተመሳሳይ  ውይይት  ከተቀሩት ዘጠኝ  የክልሉ ዞኖች ጋር በቅርቡ ይደረጋል ተብሏል::

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.