Fana: At a Speed of Life!

ኤጀንሲው በሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራት ልኳንዳ ቤቶች የስጋ አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት ዝግጅት ማድረጉን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በመጪው የገና በዓል በሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራት ልኳንዳ ቤቶች የስጋ አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህብረት ስራ ኤጀንሲ አስታወቀ።
ኤጀንሲው መጪውን የገና እና የጥምቀት በዓላት አስመልክቶ ከሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራት አመራሮችና ከ200 በላይ ከሚሆኑ የልኳንዳ ቤት ባለቤቶች ጋር ተወያይቷል።
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ውብነህ እምሩ በመጪው የገና በዓል በሸማቾች የህብረት ስራ ማህበራት ልኳንዳ ቤቶች የስጋ አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት ከህብረት ስራ ዩኒየኖች ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
በዩኒየኖች አማካኝነት የእርድ ሰንጋዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ለልኳንዳ ቤቶች እንደሚቀርብም ነው የገለጹት።
በኤጀንሲው የግብይት ዳይሬክተር ወይዘሮ ደብሪቱ ለዓለም በበኩላቸው ልኳንዳ ቤቶቹ ለህብረተሰቡ ጥራት ያለው አገልግሎት እንዲሰጡ አስፈላጊው ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን ተናግረዋል።
በበዓል ጊዜ የሚፈጠርን መጨናነቅ ለመቀነስም ቅድመ ስራዎች ከመደበኛ ሰዓት ውጪ እንደሚከናወኑ ገልጸዋል።
ልኳንዳ ቤቶች ለሰራተኞቻቸው በቂ የኮሮና ቫይረስ ጥንቃቄ ግብዓት እንዲያዘጋጁ መደረጉንም ተናግረዋል።
ህብረተሰቡ ወደ ልኳንዳ ቤቶች በሚመጣበት ጊዜ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል መጠቀምን ጨምሮ ሌሎች የጥንቃቄ መመሪያዎችን ተግባራዊ እንዲያደርግም አሳስበዋል።
የልኳንዳ ቤት ባለቤቶች በበኩላቸው÷ ከዚህ ቀደም ለእርድ የሚቀርቡላቸው በሬዎች ዋጋ ውድ በመሆኑ የስጋ ዋጋ ተመን ተመጣጣኝ እንዳልነበር አስታውሰዋል።
በህብረት ስራ ዩኒየኖች በኩል የእርድ በሬዎች በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲቀርቡ መደረጉ ልኳንዳ ቤቶች በወጣው ተመን እንዲሸጡ እንደሚያስችል መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.