Fana: At a Speed of Life!

በመተከል ዞን ለተፈናቀሉ ዜጎች እስካሁን 9 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር ድጋፍ መሠብሰቡ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 3 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በመተከል ዞን ለተፈናቀሉ ዜጎች እስካሁን 9 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር ድጋፍ መሠብሰቡን የክልሉ ድጋፍ አሰባሳቢ ዐቢይ ኮሚቴ አስታወቀ

የክልሉ ግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ኃላፊ እና በመተከል ዞን የተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ አሰባሳቢ ዐብይ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ባበክር ኻሊፋ÷ ኮሚቴው ለተፈናቀሉ ዜጎች በክልሉ 50 ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ ዕቅድ ይዞ ወደ ሥራ መግባቱን አስታውሰዋል።

በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ 9 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር መሰብሰቡን አስታውቀዋል፡፡

ኮሚቴው ከክልሉ የመንግስት ተቋማት፣ በአሶሳና ካማሺ ዞኖች፣ በማኦና ኮሞ ልዩ ወረዳ እንዲሁም በአሶሳ ከተማ አስተዳደር ከአመራሮችና ከመንግስት ሠራተኞች ባካሄደው የድጋፍ ማሰባሰብ ውይይት ጥሩ ምላሽና ድጋፍ ማግኘቱን አቶ ባበክር ገልጸዋል፡፡

የክልሉ የመንግስት ተቋማት፣ አመራሮችና የመንግስት ሠራተኞች ባደረጉት የድጋፍ ተሳትፎ 4 ነጥብ 5 ሚሊየን የተገኘ ሲሆን÷ ከአሶሳ ዞን ከ2 ሚሊየን ብር በላይ፣ ከካማሺ ዞን ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ፣ ከማኦና ኮሞ ልዩ ወረዳ ከ550 ሺህ ብር በላይ፣ ከአሶሳ ከተማ አስተዳደር ደግሞ ከ500 ሺህ ብር በላይ መገኘቱንም አቶ ባበክር አመልክተዋል፡፡

አያይዘውም ከሚቴው እስከታች በመውረድ ከህብረተሰቡ ጋር በመወያየት ድጋፍ ለማሰባሰብ ይሠራል ብለዋል፡፡

ለሁሉም የኢትዮጵያ ከፍተኛ ተቋማት የድጋፍ ጥያቄ መቅረቡን የገለጹት አቶ ባበክር÷ በክልሉ በተለያዩ ዘርፎች በኢንቨስትመንት ለተሰማሩ ባለሃብቶች እንዲሁም መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች የድጋፍ ጥያቄ ቀርቦ ምላሽ መገኘት መጀመሩን ተናግረዋል፡፡

በፌዴራልና በክልሉ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር በሚደረገው ድጋፍ ያልተሸፈኑ እጥረቶችን በመለየት የሚገኘውን ድጋፍ ለተፈናቀሉ ዜጎች በወቅቱ ለማድረስ እየተሠራ መሆኑም የኮሚቴው ሰብሳቢ ገልጸዋል፡፡

በተለያዩ አካላት ለተፈናቀሉ ዜጎች በተበታተነ መንገድ እየተደረገ ያለው ድጋፍ በአንድ ማዕከል አልፎ ለሁሉም ዜጎች እንዲደርስ ለማድረግ ኮሚቴው እየሠራ መሆኑን ጠቁመው÷ ድጋፍ የሚያደርጉ አካላትም ለዚህ የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ ማቅረባቸውን ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.