አማራ ባንክ አክሲዮን ማህበር የሼር ሽያጭ ጊዜውን እስከ የካቲት 30 ድረስ አራዘመ
አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 30 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስረታ ላይ የሚገኘው አማራ ባንክ አክሲዮን ማህበር የሼር ሽያጭ ጊዜውን እስከ የካቲት 30 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ማራዘሙን አስታወቀ።
ባንኩ የአክሲዮን ሽያጩን በውጭ ሃገር የሚኖሩ ዜጎች እና ባለሃብቱ የመግዛት ፍላጎት ማሳየታቸውን ተከትሎ ማራዘሙን የባንኩ አደራጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ መላኩ ፈንታ ተናግረዋል።
ካለፈው ነሃሴ 11 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ በተፈጸመ የሼር ሽያጭ ከ70 ሺህ በላይ ግለሰቦች እና ድርጅቶች ሼር መግዛታቸውም ተጠቁሟል።
ከሽያጩ ውስጥ ከ4 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በላይ የተፈረመ ሲሆን፥ 3 ቢሊየን ብር ደግሞ መከፈሉንም ሰብሳቢው ገልጸዋል።
ባንኩ አሁን ላይ ያራዘመው የሼር ሽያጭ ጊዜ የመጨረሻው መሆኑንም አስታውቀዋል።
በይስማው አደራው