Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ የደምቢዶሎ- ሙጊ- ዶላ አስፓልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታን አስጀመሩ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የደምቢዶሎ- ሙጊ- ዶላ አስፓልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ማስጀመሪያ ስነስርአት ተካሄደ።

ግንባታውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፥ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፥ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው፣ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰመስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ እና ሌሎች የስራ ሀላፊዎች በደምቢዶሎ ከተማ በመገኘት አስጀምረዋል።

መንገዱ 50.9 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን በፌዴራል መንግስት ወጪ በ1.6 ቢሊየን ብር ይገነባል።

ግንባታውን በሶስት አመት ተኩል ለማጠናቀቅ ኮንትራት የወሰደው የቻይናው ሬይልዌይ ሰቨንስ ግሩፕ ነው።

ደበሌ ጋረደው

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details… በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.