Fana: At a Speed of Life!

በአጅባር ከተማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን የሚደግፍ ሰልፍ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአምሐራ ሳይንት ወረዳ የአጅባር ከተማና የአጎራባች ቀበሌ ነዋሪዎች በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አመራር ሰጭነት የመጡ ለውጦችን ለመደገፍ ያለመ የድጋፍ ሰልፍ በዛሬው ዕለት አካሂደዋል፡፡

ነዋሪዎቹ “ለውጡን የሚያደናቅፍ የሴራ ፖለቲካ እናወግዛለን”፣ “ፈተናዎችን በጋራ እየመከትን የለውጡን ዘላቂነት እናረጋግጣለን”፣ “ጽንፈኝነት የሠላምና የአብሮነት እሴት ጸር ነው”፣ “ሠላምና የሕዝቦች አንድነት ይለመልማል”፣ “ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የጁንታውን ቡድን ለማምከን የሠጡትን በሳል አመራር እናደንቃለን” እና መሰል መልእክቶችን ማስተላለፋቸውን የወረዳው የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.