Fana: At a Speed of Life!

125ኛው የአድዋ ድል በዓል በአሶሳ ከተማ ተከበረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)125ኛው የአድዋ ድል በዓል በአሶሳ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል።
በዓሉ በተከበረበት ወቅት የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ወይዘሪት ምስኪያ አብደላ የአድዋ ድል ለሀገር ዳር ድንበር መከበር እምነት፣ ቋንቋ፣ ዘር፣ አስተሳሰብና ጾታ ሳይለያቸው የአገር ፍቅር ከሩቅም ከቅርብም የጠራቸው ኢትጵያውያን ወራሪውን የጣሊያን ጦር ድባቅ የመቱበት የደምና የአጥንት ክፍያ ዋጋ ነው ብለዋል።
የአሁኑ ትውልድም ጀግኖች አባቶቻችን መስዋዕትነት ከፍለው ያስረከቡትን ሀገር እርስ በእርስ በመደጋገፍና በመተባበር፣ ከአባቶቻችን በወረስነው ወኔና መንፈስ በድህነት ላይ በመዝመት ተባብሮና ጠንክሮ በአንድነት ለሀገር ሠላምና ደህንነት ዘብ በመቆም እና በልማቱ ዘርፍ የበኩሉን ሚና በመጫወት ይሄንን የድል በዓል ማክበር እንደሚጠበቅበት ተናግረዋል፡፡
የአሶሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ዑመር መሐመድ በበኩላቸው የአድዋ ድል ኢትዮጵያዊያን በጊዜያዊ ችግርና መከራ ተሸንፈው እጅ መስጠትን እና ተስፋ መቁረጥን ሳይሆን ችግርን ተጋፍጠው አንገት ለአንገትም ተናንቀው ድልን በመቀዳጀት አሸናፊነትን እና አይበገሬነትን ለዓለም ሁሉ ህያው ምስክር መሆን የቻሉበት ዘመን አይሽሬ የድል በዓል መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.