Fana: At a Speed of Life!

የ2013/14 የምርት ዘመን የአፈር ማዳበሪያ በወቅቱ የማጓጓዝ ስራ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 25 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የ2013/14 የምርት ዘመን የአፈር ማዳበሪያ በወቅቱ የማጓጓዝ ስራ እየተሰራ  መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በግብርና ሚኒስቴር የግብርና ግብዓት አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መንግስቱ ተስፋ ÷በዘንድሮው የምርት ዘመን 18 ነጥብ 1 ሚሊየን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ግዢ ለመፈፀም እና ለአርሶ አደሩ ለማሰራጨት በማቀድ ሙሉ በሙሉ ግዢ መፈፀሙን ገልፀዋል፡፡

ግዢ ከተፈፀመው የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ 5 ነጥብ 7 ሚሊየን ኩንታል የሚሆነው ጅቡቲ ወደብ የደረሰ ሲሆን ከዚህ ውስጥም 5 ነጥብ 6 ሚሊየን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሃገር ውስጥ ማጓጓዝ ተችሏል፡፡

ይህም ጅቡቲ ወደብ ከደረሰው የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ 98 በመቶ የሚሆነውን ወደ ሃገር ውስጥ ማስገባት መቻሉን ነው የገለጹት፡፡

አጠቃላይ እንደ ሃገር ከታቀደው 18ነጥብ 1 ሚሊየን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ውስጥም 31 በመቶ የሚሆነውን ማጓጓዝ ተችሏልም ነው ያሉት፡፡

አቶ መንግስቱ አክለውም ወደ ሀገር ውስጥ ከገባው የአፈር ማዳበሪያ 3 ነጥብ8 ሚሊየን ኩንታል ወደ ህብረት ስራ ማህበራት የተጓጓዘ ሲሆን አሁን ካለው የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ 50 በመቶ የሚሆነው ወደ ህብረት ስራ ማህበራት የተሰራጨ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ወደ ተጠቃሚው አርሶ አደርም  656 ሺህ 768 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ የተሰራጨ ሲሆን ወደ ህብረት ስራ ማህበራት ከተጓጓዘው ውስጥ 16 ነጥብ 8 በመቶ የሚሆነውን ለአርሶ አደሩ ማቅረብ እንደተቻለ የገለፁ ሲሆን ÷በቅርብ ጊዜ ውስጥም ሁሉንም የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት ለአርሶ አደሩ በወቅቱ እንዲደርስ ይደረጋል ብለዋል፡፡

የዘንድሮው የአፈር ማዳበሪያ ካለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር የ3 ኘትብ1 ሚሊየን ኩንታል ብልጫ እንዳለውም ነው ያመለከቱት፡፡

ባለፉት አመታት በአፈር ማዳበሪያ ግዢና የማጓጓዝ ስራ ላይ ይስተዋሉ የነበሩ ችግሮችን በመለየት እንዲሁም ውጤታማ ስራ የሰሩና ትልቅ ሚና የተጫወቱ ባለድርሻ አካላትን የማመስገንና እውቅና የመስጠት ስራ መሰራቱን አስታውሰዋል።

በዚህም ምክንያት ካለፉት አመታት የተሻለ ስራ መስራት መቻሉን ጠቁመው÷ በያዝነው የምርት ዘመን የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ቀድሞ በማጠናቀቅ የአፈር ማዳበሪያው በወቅቱ አርሶ አደሩ ጋር እንዲደርስ የሚያስችል ስራ ተሰርቷል ብለዋል፡፡

በዘንድሮው አመት የአፈር ማዳበሪያ ዋጋ በመጨመሩ ምክንያት መንግስት 4 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ድጎማ በማድረግ የአፈር ማዳበሪያ ግዠው መፈጸሙን ከግብርና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.