በርካታ የስልክ ገመዶችን አከማችተው የተገኙ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮ-ቴሌኮም ንብረት የሆኑ በርካታ የስልክ ገመዶች በስርቆት አከማችተው የተገኙ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ።
ከመሬት ውስጥ ተቆፍረው የወጡ የስልክ ገመዶችን አከማችተው የተገኙ ሁለትተጠርጣሪዎች በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ መርካቶ ጋዝ ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል።
በተመሳሳይ መርካቶ ኢትዮጵያ ዳቦ ቤት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አንድ ተጠርጣሪ በመሬት ውስጥ የተቀበሩ የኢትዮ ቴሌኮም ንበረት የሆኑ የስልክ ገመዶችን ቆፍሮ እያወጣና እየቆረጠ ሰርቆ ለመውሰድ ሲሞክር በቁጥጥር ስር መዋሉን የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡
በአሁኑ ወቅትም ወንጀሉን በፈጸሙት ተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑ ተመላክቷል።