በአማራ ክልል ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች የመጀመሪያ ዙር የሰብዓዊ ድጋፍ እየቀረበ ነው-ሰላም ሚኒስቴር
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአማራ ክልል ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች ከክልሉ በቀረበ ጥያቄ መሰረት የመጀመሪያ ዙር የሰብዓዊ ድጋፍ ከሚያዝያ 10 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ የመጀመሪያ ዙር የሰብዓዊ ድጋፍ እየቀረበ መሆኑን የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ።
ሚኒስቴሩ በዜጎች ላይ የተሰነዘረን ጥቃት ተከትሎ የህግ የበላይነትን የማረጋገጥ ስራና የዕለት ደራሽ ሰብዓዊ ድጋፍ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠሉን ገልጿል።
ከክልሉ በቀረበ ጥያቄ መሰረት የመጀመሪያ ዙር የሰብዓዊ ድጋፍ ከሚያዝያ 10 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ እንዲዳረስ እየተደረገ ሲሆን ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ወገኖቻችንን ወደ ቀዬአቸው ለመመለስና መልሶ ለማቋቋም በልዩ ትኩረት እየተሰራ ይገኛል ሲል በፌስቡክ ገፁ ባወጣው መግለጫ ላይ አስፍሯል።
ያጋጠሙ ችግሮችና በዜጎች ላይ የተፈጸሙ አሰቃቂና አሳዛኝ ጥቃቶችን በተመለከተ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ የተጀመረው የምርመራ ስራ እንዲሁም በአካባቢው ጸጥታ የማስፈን ተግባራት የሚመለከታቸው የፌደራልና የክልል አካላት በቅንጅት እያከናወኑ ይገኛሉ ነው ያለው
በቀጣይም ዜጎችን በፍጥነት የማቋቋሙ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፦https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!